ቁጥር.2.

የጥንታዊቷ ግሪክን የልጆች ወሲባዊ ጥቃትን ልማድ የአር.ኤፍ.ኤል.ኤም ማዳነቅ


ከአር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. ድረ-ገጽ የተወሰደ፡-

ያኔና አሁን  

በጥንታዊት ግሪክ ውስጥ በሽማግሌዎችና ወጣቶች ወንዶች መካከል ያለ መፈቃቀር ተቀባይነት ነበረው፡፡ እንዲህ ማለቱ ትክክል ባይሆንም ነገር የወጣት ወንዶች የህይወታቸው ዓላማ እርስ በርሳቸው እንዲጋቡ ስለነበር እድሜ ዘለቅ ግብረ ሰዶማዊነት የኅብረተሰቡ ልማድ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ለሴቶችም ሆነ ለባሪያዎች ተነጻጻሪነት ያለው የግብረ ሰዶማዊነት ፎርም አልነበረም፡፡ ስለሆነም እንዲህ መሰሉ ግብረ ሰዶማዊነት የሚያንፀባርቀው የወንዶች የበላይነት የታየበትን ጥንታዊውን ኅብረተሰብ ነው፡፡

ከክርስቶስ ልደት በፊት በ5ኛ ክፍለ ዘመን ሌስቦስ በምትባል የግሪክ ደሴት እንስት የግጥም ጸሐፊ የሆነች ሳፕፎ በርካታ ወጣት ልጃገረዶችን ታስተምር ስለ ነበር ሌዝቦስ የሚለው የከተማው መጠሪያ ለእንስት ግብረ ሰዶማዊነት መጠሪያነት ውሏል፡፡ የእንግሊዘኛው ልዝቢያን የሚለው ቃል የተወረሰው ከዚሁ የግሪክ ቃል ነው፡፡

የክርስትና ሃይማኖት ግን በፆታ ግንዛቤ ረገድ አዲስ አመለካከትን አምጥቷል፡፡ በክርስትና እምነትም ውስጥ ብዙ ተባዙ የሚለው የፍጥረት ሕግ ስለ ተቀመጠ ልቅ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ምኞት የተኮነ ነው፡፡ የግብረ ሰዶማዊነት ድርጊቶች ሁሉ ም የፍጥረትን ሥርዓት የሚሽሩ በመሆናቸው ኀጢአት ተደርጎ ይታያል፡፡ ከአር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. (RFSL)የተጠቀሰ፡፡

የጥንታዊ የግሪክ ኅብረተሰብ ‹‹በሽማግሌና ወጣት ወንዶች መካከል ያለውን መፈቃቀር በጣም ያደንቃል›› ማለቱ አር.ኤፍ.ኤስ.ኤል. ደርጅት እንዴት ያለ ቅናት ያደረበት እንደሚመስል ልብ በሉ፡፡ እዚህ ላይ በግልጽ የምንነጋገረው ነገር በጥንታዊቷ ግሪክ በልጆች ላይ የሚደረግ የወሲብ ጥቃት በጣም የተስፋፋ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ክርስትና በጻታዊ ግንኙነት ላይ አዲስ ግንዛቤ በማምጣቱ አር.ኤፍ. ኤፍ. ኤል. ሊያዝን ይችላል፡፡ ምናልባትም ልቅ የግብረ-ስጋ ሥጋ ምኞትና በልጆች ላይ የሚደረግ የወሲብ ጥቃት /ፔደፊሊያ/ የኅብረተሰቡ ልማዶች የሚሆኑበትን ዘመን የሚናፍቁ ይመስለኛል፡፡

በእርግጥም ክርስትናም የያንዳንዱ ግለሰብ እሴት ተገቢ ትኵረት የሚያገኝበትን አዲሱን ገፅረተ-ዓለም አምጥቷል፡፡ ክርስትናም ለግዲያተርስ ትዕይንት ፍጆታ የሚውለውን የሰው ሥጋ መሥዋዕትን አስቀርቷል፡፡ ባርነት እንዲቆም፣ ሽማግሌ ወንዶች ከፍተኛ እሴት የሰጡትን የግል ና ልቅ ወሲባዊ ፍላጎት እርካታቸውን ና ወጣት ወንዶች ላይ ያተኮረውን አቋማቸው እንዲቀር አድርጓል፡፡ ሴቶች በከፍተኛ አክብሮት እንዲያዙና የሰው ሕይወት አጠቃላይ ክብር እንዲኖረውና ሥር እንዲሰድድ አድርጓል፡፡ የቤተሰብ ሕይወት መሰረት የሆኑት እናትነት፣ አባትነትና ልጅነትየኅብረተሰብ ጤናማ ማዕዘን እየሆኑ መጡ፡፡ በጥንታዊ ግሪክ ኅብረተሰብ ዘንድ ተፈላጊ ከነበረው ‹‹በሽማግሌዎችና በወጣቶች መካከል ካለው ፍቅር ይልቅ በባልና ሚስት መካከል የሚደረግ የፆታ ግንኙነት ታማኝነት ተፈላጊ የኅብረተሰብ የኑሮ ሥርዓት ሆነ፡፡

በዚህ በአዲሱ የክርስቲያናዊ ሥልጣኔ ሰዎች ሰለሚያደርጉት ሥራ ሁሉ በፈጣሪያቸው ፊት ስለሚገጥማቸው ተጠያቂነት በማሰብ ለግብረገባቸውና ለሥነ ምግባራቸው ከፍተኛ እሴት መስጠት ጀመሩ፡፡ ይህም ኀላፊነት በሕይወታቸው ዘመን ለቤተሰባቸውም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ስላሰዩት ተግባር ተጠያቂነትን ሃላፊነት የሚወስዱበት ነው፡፡ ያም ሆኖ ያለፉት 2000 ተከታታይ ዓመታት ፍጹማን አልነበሩም፡፡ የሐይማኖቶች ጦርነቶች /ክሩሴድስ/ የባርነት ዘመን፣ የመካከለኛው የጨለማ ዘመን፣ ሰካራምነትና ባጠቃላይ የሞራል ውድቀት የነበረባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ በነዚያ በ2000 ዓመታት ሥልጣኔያችን ንጽረተ-ዓለማችን ሁሌም ቢሆን የሞራል ውድቀትና ውርደትን ዘመናትን ሊያርም በሚያስችል ጠንካራ እሴት ላይ የተመሠረተ ነበር፡፡ ነገር ግን በዘመናችን በምዕራቡ ዓለም አይተነው የማናውቀው አስገራሚ ለውጥ ታይቷል፡፡

የአሁኑ ሥልጣኔ ማለቂያ ይሆን;
አሁን ደግሞ በ2000 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞራል ውድቀትና ውርደት እንዴት ወደ ተፈላጊነትና ወደ አስደሳችነት ከፍ እያለ እንደመጣ እናያለን፡፡ በዚህ በበጋው ወራት መጨረሻ ላይ በአገራችን ታላቁና ዕለታዊ ጋዜጣ ‹‹ዘ ዴይሊ ኒውስ›› ላይ በዚህ በበጋ ወራት በትዳር ጓደኞቻቸው ላይ ስለ ሠሩት የእምነት ማጉደል ታሪክ ለጋዜጣው ደብዳቤ እንዲጽፉ ለአንባቢዎች ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ይህ ነገር ሆነ ተብሎ የተጻፈው አብዛኞቹ የጋዜጣው አንባቢዎች አስደናቂ የተባለለት ይህ ወሲባዊ ፍላጎትና ልቅ የግብረ ሥጋ ምኞት ታሪኮችን በማንበብ እንዲደሰቱ ለማድረግ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት የማይፈለጉ ነገሮች ሁሌም አሉ፡፡ ግን ሥልጣኔያችን ዛሬ ይህንን ድርጊት ቦታ ሲሰጠው ማየት ከዚህ ቀደም ያልነበረ ነገር ነው፡፡ ላለፉት 2000 ዓመታት በጠንካራነት ያገለገለን ቤተሰባው መዋቅር ዛሬ በዓይናችን ፊት አየፈራረሰ ይታያል፡፡ ስለሆነም ረጅም ዘመን ያስቆጠረው ሥልጣኔያችን ወደ መጨረሻው መቃረቡን እያየን ነው፡፡

ለነገሩ አርቀን ካየነው ሥልጣኔ እስከ ዘላለም አይቆይም፣ስልጣኔ ይመጣል ይሄዳል:: ስለሆነም ልንገረም አይገባም፡፡ ነገሩ ዙር-ገጠም ነው፡፡ እያንዳንዱ ሥልጣኔ በኋላ ቀር ልምድና አስተሳሰብ ይጀመርና በአምባ ገነንነት ይታጀባል፡፡ ያኔ ሕጎች ሁሉ አኗኗርን ለመምራት ያላቸው አቅም ይቀንሳል፡፡ በጅማሬው የሆነ ዓይነት አምባገነናዊነት ይሆንና ከዚያ ወደፖለቲካዊ ነጻነት፣ ወደ ሰብዓዊ ህይወት ክብር ተቆርቋሪነት ና በእርስ በርስ መከባበርና በመረዳዳት ላይ ወደተገነባ ና ያፈራቸውን ፍሬዎች ህብረተሰቡ ወደሚያጭድበት የተደራጀ ስልጣኔ ደረጃ ይዘልቃል፡፡ ነገር ግን ስስት ቀጥሎም ስንፍና ና አጠቃላይ የስራ ፍቅር ማጣት ጣልቃ ይገባል፡፡ ቀጥሎም የሞራል ውድቀትና ቅናት ቤተሰብን ያፈራርሳሉ፡፡ እኛም ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ይህንኑ ይመስላል፡ ሥልጣኔያችን ወደሚፈራርስበት፣ ወደ ኋላ ቀርነት የምንጓዝበትና የሥልጣኔያችን ዙር ወደሚዘጋት ጊዜ የደረስን ይመስላል፡፡