ቁጥር.3

ግብረ-ሰዶማውያን ሁልጊዜም የልጆች ወሲብ ጥቃት ወዳጆች ናቸውን?


ይህ ጥያቄ የዩንሾፒንግ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በጃንዋሪ 19 ቀን 1005 ባስቻለው ችሎት የፓስተር ኦክ ግሪን ክስ በመረመረበት ጊዜ በዓቃቤ ሕጉ በኩል ቀርቦ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕጉ ቬል ይንግቬንሰን ግብረ ሰዶማውያን ሁሌም ቢሆን በልጆች ላይ ወሲባዊ ጥቃት የማድረስ ዝንባሌ ያላቸው (ፔዶፊሊያዎች) ናቸው ለማለት የሚያስደፍር አንዳችም ሳይንሳዊ ማስረጃ የሌለውና ከግብረ ሰዶማውያን ይልቅ ግብረ ሰዶማውያን ያልሆኑት /ሄትሮሴክሹዋልስ/ ግን ወደ ልጆች የወሲባዊ ጥቃት ብዙ የማዘንበል ፍላጎት ይታይባቸዋል ብሏል፡፡ እንዴት ያለ እርባና የሌለው፣ እውነተኛ ያልሆነ ውሸት ያዘለ ንግግር ነው!!

ለጥያቄው የሚሰጠው ትክክለኛ ምላሽ ከሕዝብ ፖሊሲ አንጻር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆን ነበረበት፡፡ ግብረ ሰዶማውያን ያልሆኑ /ሄትሮሴክሹዋልስ/ አብዝተው ወደ ልጆች የወሲባዊ ጥቃት ብዙ የማዘንበል ፍላጎት ይታይባቸዋል ከተባለ ጉዳዩ ለግብረ ሰዶማውያን የተወሰኑ የሥራ ቦታዎችና ተግባራት ሊያዙላቸው ይገባል እንደ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ልጆችን ለተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ልምምድ ማደፋፈር እንዲቻል ግብረ ሰዶማውያን በሙዓለ-ሕፃናት፣ ቦይ-ስካውት ልጆችን ወደ አዳር የካምፕ ጉዞዎች የመውሰድን ሥራ ይሥሩ እንደ ማለት ነው፡፡ ነገሩን በግልባጩ ካየነው ግን መልኩ ሌላ ነው፡፡

በዋነኛው ጽሑፌ ውስጥ ግብረ ሰዶማዊ ካልሆነ ማንኛውም ወንድ (ሄትሮሴክሹዋል) ይልቅ ግብረ ሰዶማዊ የሆነ ማንኛውም ሰው አብልጦ የልጆች ወሲባዊ ጥቃት አፍቃሪ /ፔዶፋይል/ ሊሆን እንደሚችል በጣም ጠንካራ ማስረጃዎችን በዋናው ጽሁፌ ውስጥ አቅርቤዋለሁ፡፡ በአዕምሮአቸው ብስለት ታማኝነት ካላቸው ሰዎች ጋር የምንነጋገር ከሆነ ሐቅ ምን ጊዜም ሐቅ በመሆኑ ከፖለቲካዊ ትክክለኛነት ጋር ለመስማማት ስንል ልንሸፍነው አይገባውም፡፡

ከዚህ በታች ደግሞ በሌላ የመረጃ ምንጭ (ዳታ ቤዝ) ላይ የተመሰረተ ትንታኔ አለ፡፡ ልምዱ በሁሉም ዘንድ ያለ ቢሆንም በአንዳንድ ጉልህ ምክንያቶች የተነሳ ትክክለኛ ቁጥሮች ላይ ለመድረስ አስቸጋሪነት አለው፡፡ በልጆች ላይ የሚደረግ የወሲብ ጥቃት (ፔደፋይል) እስካሁንም ድረስ ወንጀል ነው፡፡ ለወንጀሉ ሰለባ የሆኑት የሆኑት ሰዎች እንዴት ሪፖርት እንደሚደረግ ስለማያውቁ ወንጀሉ በእስታቲስቲክስ ሳይመዘገብ እስካሁን ድረስ እንደቀጠለ ነው ፡፡ ስለሆነም በልጆች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ያደረሰ ሰው በተያዘ/ዘች ጊዜ የትኛው ዓይነት ፆታዊ ግንዛቤ እንዳለው/ዳላት ለማረጋገጥ ሁሌም አስቸጋሪ ነው፡፡ እንደኛ ባለው ፖለቲካዊ ትክክለኛነትን በሚከተል ኅብረተሰብ ውስጥ ነገሩ ሁሌም ተነስቶ አይታወቅም፡፡

ወንድም ይሁን ሴት በየጾታቸው አንፃር ያሉትን ልጆች በወሲባዊ ጥቃት ይደፍራሉ፡፡ ስለሆነም አራት ዓይነት የወሲባዊ ጥቃት ቅንጅቶች አሉ፡፡ ከአራቱ ወሲባዊ ጥቃት ቅንጅቶች መካከል ሁለቱ ማለትም /ሴት ወጣት ወንድ ልጅን፣ ወንድ ደግሞ ልጃገረድን/ የመድፈር ድርጊቶች የሚፈጸሙትም በተለይ ግብረ-ሰዶማውያን ባልሆኑ ሰዎች /ሄትሮሴክሹዋልስ/ በመሆኑየተቃራኒ ጸታ ግንዛቤ(ሄትሮሴክሹዋል ኦሪየንቴሽን) ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በተመሣሣይ ሁኔታ ሌሎቹ ሁለቱ ማለትም /ሴት ልጃገረድ በአዋቂ ሴት/ እና / ወጣት ወንድ በአዋቂ ወንድ/ የተደረጉት ወሲባዊ ጥቃቶች የተከናወኑት ግብረ ሰዶማዊ ፆታዊ ግንዛቤ (ሆሞሴክሹል ኦሪየንቴሽን ) ባላቸው ሰዎች ነው፡፡

  ታዲያ በአብዛኛው የተለመደው ድርጊት የትኛው ነው; የተቃራኒ-ጾታ ወሲባዊ ጥቃት ወይንስ የተመሳሳይ ጾታዊ ወሲባዊ ጥቃት; የአሜሪካ መንግሥት የፍትህ ቢሮ ( ቢሮ ኦፍ ጀስትስ) የእስታቲስቲክስ ጸ/ቤት እ.ኤ.አ.- ከ1991-1996 ድረስ ባሉ ዓመታት መካከል በ12 የአሜሪካ ግዛቶች / በአላባማ፣ ኮሎራዶ፣ አይዳሆ፣ ኤሌኖይ፣ አይዋዋ ማስቹሴትስ፣ ሚሺጋን፣ ኖርስ ዳኮታ፣ ሳውዝ ካሮላይና፣ ኡታህ፣ ቬርሞንት፣ ቨርጂኒያ/ ላይ እ.ኤ.አ.- በ2000 ዓ.ም. መጠነ ሠፊ ጥናት አድርጎ ነበር፡፡ እነዚህ የአሜሪካ ግዛቶች የአገር አቀፉ ናሽናል ክራይም ቪክቲማይዜሽን ሰርቬይ የሚባለው ድርጅት አካል ስለነበሩ የመረጃው ምንጩ /ዳታቤዝ/ ኤን.ኤይ.ቢ.አር.ኤስ /ናሽናል ኢንሲደንት -ቤዝድ ሪፓርቲንግ ሲስተም/ በመባል ይታወቃል፡፡ የጥናቱ መጠሪያ ( ሴክሹዋል አሶልት ኦፍ ያንግ ችልድረን አዝ ርፖርትድ ቱ ዘ ሎው ኢንፎርስሜንት ) ቪክቲም ኢንሰደንት ኤንድ ኦፌንደር ካራክተርስቲክስ›› በመባል ይታወቃል፡፡ ጥናቱን የመሩት ዶ/ር ሃዋርድ ስናይዳር ሲሆኑ በማጣቀሻ.11 ላይ ተጠቅሶአል፡፡ ደጋፊ መረጃም በማጣቀሻ. 12 ላይ አለ::

በጥናቱ ውስጥ የተገለጹ ዋና ዋና ሐሳቦች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ከ57762 በሰለባዎቹ ተለይተው በሚታወቁ ወንጀለኞች የተደረጉ የወሲብ ጥቃቶች ውስጥ

- በጉልበት መድፈር 42%

- የግዳጅ ሰዶማዊ ድርጊት 8%

- በቁሳቁስ የተደረገ ወሲባዊ ጥቃት 4%

- በኀይል የተደረጉ የሰውነት መነካቶች 45%

 2. ለሕግ አስከባሪዎች በቀረበው ሪፖርት መሠረት ወሲባዊ ጥቃት ካደረሱት ተከሣሾች 96% ወንዶች ናቸው፡፡ ስለሆነም እንደ አሳማኝ ግምት ብንቆጥረው ቀሪው 4% የሚሆኑት ሴቶች እንደ 96% ወንዶች ተመሳሳይ ዓይነት ምድብ ውስጥ እንዳሉ እንገምት፡፡ ‹‹በጉልበት መድፈር›› የሚለው ምድብ ግብረ ሰዶማውያን ያልሆኑ /ሄትሮሴክሹዋልስ/ አዋቂ ወንዶች የሚደርጉትን ወሲባዊ ጥቃት የሚገልጥ ሲሆን ‹‹የግዳጅ ሰዶማዊ ድርጊት›› የሚለው ምድብ ደግሞ ግብረ ሰዶማውያን (ሆሞሴክሹዋል) የሆኑ ሰዎች የሚያደርጉት የግንኙነት አደፋፈር ነው ማለት ነው፡፡

3. በቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት የምድቡ መቶኛ /ካቴጎሪስ/ ውስጥ ያሉት በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ስብስብ ነው፡፡ ከ18 ዓመት እድሜ በታች ባሉ ልጆች ላይ ከተደረጉት ወሲባዊ ጥቃቶች መካከል ጥቂቶቹን የግንኙነት ጥቃቶችን ብንመለከት በሪፖርቱ የመጀመሪያው ሰንጠረዥ/ሪፖርት 1/ላይ 45.8% ‹‹በጉልበት መድፈር›› የተደረገባቸው በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ፡፡ 78.8% ‹‹በኀይል የተደረገ ሰዶማዊ ድርጊት›› የተደረገባቸው በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ፡፡ 75.2% ‹‹በቁሳቁስ የተደረገ የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው በዚሁ የዕድሜ ከልል ውስጥ ያሉ ፡፡ 83.8% ‹‹በኀይል የተደረጉ የሰውነት መነካካቶች›› የተደረገባቸው በዚሁ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሆነው እናገኛቸዋለን፡

ከ100% ውስጥ 54.2% ማለትም (=100%-45.8%) ‹‹በኀይል የመደፈር ድርጊት›› ከ18ና ከዚያም በላይ እድሜ ባላቸው ሴቶች ላይ የደረሰ ሲሆን 21.2% ዕድሜያቸው ከ18ና ከዚያ በላይ በሆኑ ወንዶች ላይ የተደረገ ሰዶማዊ ጥቃት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በርግጥ የሚያመለክተው ሴቶች አሁንም ቢሆን አሰገድዶ መድፈር ጥቃት የተጋለጡ መሆናቸውን ነው፡፡ ግብረ ሰዶማውያን ባልሆኑ ሰዎች በኩል የሚደረገው ጥቃት ተጠቂዎቹ ሴቶች መሆናቸውን ሲሆን በዚህ እድሜ ያሉ ወንዶች ደግሞ የሚደርስባቸውን ማንኛውም አካላዊ ጥቃት ሁሉ በከፍተኛ ደረጃ ለመከላከል የሚችሉበት ዕድሜ መሆኑን ነው፡፡

4. በቁጥር 3 ላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች መጠን ከቁጥር 1 ላይ ከደረሱት ጋር አያይዘን ስንመለከት ደግሞ የሚከተለውን እናገኛለን፡፡ ከ ሰንጠረዝ 1-45.8% X 42% = ከጠቅላላው የወሲብ ጥቃቶች 19.2% ዕድሜያቸው ከ18 በታች በሆኑ ልጃገረዶች ላይ የደረሰ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ነው፡፡ ያም ማለት የተቃራኒ ጾታ ወሲባዊ /ሄቶሮሴክሹዋል ሞልስቴሽን/ጥቃት ነው ማለት ነው፡፡ ከሰንጠረዥ 1 ደግሞ ከጠቅላላው የወሲብ ጥቃት ቁጥር ውስጥ 6.3% ማለትም ( 78% X 8% =) ዕድሜያቸው ከ18 በታች በሆኑ ወጣት ወንዶች ላይ የተፈጸመ የግዳጅ ሰዶማዊ ጥቃት /ሆሞሴክሹዋል ምልስቴሽን/ ነው፡፡ 37.7% ማለትም 83.3% X 45% = ደግሞ ዕድሜያቸው ከ18 በታች በሆኑ በወንዶችና በልጃገረዶች ላይ የተደረገ ሰውነትን በኀይል የመነካካት /ሆሞሴክሹዋል ወይም ሄትሮሴክሹዋል ሞልስቴሽን/ ጥቃት ነው፡፡ በሪፖርቱ ውስጥ በተገለጠው እስታቲስቲካዊ መረጃ መሰረት በ‹‹ቁሳቁስ የሚደረግ ወሲባዊ ጥቃት›› ም ሆነ ‹‹ሰውነትን በኀይል የመነካካት(ፎንድሊንገግ) ጥቃት ውስጥ ምን ያህሉ በልጃገረዶች ወይንም በወንዶች ላይ እንደተደረጉ በትክክል ማረጋገጥ አይቻልም፡፡

በእጃችን ያለውን እስቲ እንመልከት፡፡ ከሁሉም ወሲባዊ ጥቃቶች መካከል 19.2% በእርግጠኝነት ግብረ ሰዶማውያን ባልሆኑ ሰዎች የተደረገ የልጆችን ወሲባዊ ጥቃትን /ሄትሮሴክሹዋልስ ሞልስቴሸን/ ሲያመለክት ከሁሉም ወሲባዊ ጥቃቶች መካከል 6.3% ደግሞ በእርግጠኛነት በግብረ ሰዶማውያን በኩል የተደረገ የልጆችን ወሲባዊ ጥቃትን ያመለክታል፡፡ ይህም በንጽጽር ሲታሰብ (19.2/6.3) ማለትም 3.1 ሲያመለክት በልጆች መደፈር ጉዳዮች መካከል ከአራቱ አንዱ /25%/ በግብረ ሰዶማውያን የተደረገ መሆኑን ሲገልጥ 75% ደግሞ ግብረ ሰዶማውያን ባልሆኑ ሰዎች /ሄትሮሴክሹዋልስ/ በኩል መደረጉን ያመለክታል፡፡ ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ ግብረ-ሰዶውያኑ ግብረ-ሰዶማውያን ካልሆኑት(ሄትሮሴሹዋልስ) ስንት ስንተኛ እንደሆኑ ንጽጽሩን ብንፈልግ ልዩነቱ አገር ከአገር እንዲሁም ከአንድ የሠው ልጅ ሥልጣኔ ዘመን ከሚቀጥለው በሰፊው ይለያያል፡፡ ከላይ እንዳየነው የስታቲስቲክ መረጃው (ዳታቤዝ) የተገኘው ከ1991-1996 ባሉት ዓመታት በ12ቱ የአሜሪካ ግዛቶች በተደረገው ጥናት መነሻነት ስለሆነ በእነዚህ ጊዜያት ከጠቅላላው ህዝብ መካከል ከ2-3% የሚሆነው ሕዝብ ግብረ ሰዶማዊ ( ሆሞሴክሹዋል) መሆኑን ያመለክታል፡፡ የዚህነ ክስተት አማካዩን 2.5% ብንወስድ በልጆች ላይ ከደረሰው ወሲባዊ ጥቃት ውስጥ 25 % ከጠቅላላው ህዝብ መካከል 2.5% በሚሆኑ ግብረ ሰዶማውያን በሆኑ ሰዎች የተደረገ መሆኑን ያመለክተናል፡፡

በሌላ በኩል ይህንኑ የአሠራር በመጠቀም‹‹እስታቲስቲካዊ አማካይ ግብረ-ሰዶማዊ ሰው›› ግብረ- ሰዶማዊ ካልሆነ ሰው ይልቅ በአስር እጅ በልጆች ላይ ወሲባዊ ጥቃት ፈጻሚዎች ሊሆን እንደሚችሉ ይጠቁመናል፡፡

ከላይ እንደተገለጸው ይህ ድምዳሜ የተመሰረተው በአሜሪካ አገር በ12ቱ ግዛቶች ለ6 /ስድስት/ ዓመታት ‹‹በአስገድዶ መድፈር››ና በአስገድዶ የሰዶም ጥቃት የሚደረግ ጥቃቶች ላይ ከተመዘገቡ የወንጀል ሪኮርዶች ላይ በተደረገ የንጽጽር ጥናት መሠረት ነው፡፡ ውጤቱም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሌሎች ምንጮች ከሰጡት አስተያየት ጋር ይስማማል፡፡ ለምሳሌ ያህል ጆን ዶረቲ በቅርብ ጊዜ የጻፉት ‹‹ፒደፊሊያ ሞር ኮመን አሞንግ ጌይስ›› /ማጣቀሻ. 38/ ማመሳከር ይቻላል፡

አንድ ሰው እነዚህ ቁጥሮች እንዴት ትክክለኛ እንደሆኑ ሊከራከር ይችላል፡፡ በእርግጥም የእነዚህ ቁጥሮች ትክክለኛነት የተረጋገጠ የመረጃ አቅርቦት ና ለጥናቱ የተመረጠው አሠራር /ሜቴደሎጅ/ ይወስነዋል፡፡ ነገር ግን ግብረ ሰዶማውያን ወንዶች (ሆሞሴክሹዋል) ከግብረ ሰዶማውያን ካልሆኑት ወንዶች /ሄትሮሴክሹዋል/ ይልቅ እጅግ በሚበልጥ መልኩ የልጆች ወሲባዊ ጥቃት አድራሾች /ፔደፋይልስ/ ለመሆናቸው ምንም ውይይት አያስፈልገውም፡፡ የተገኘው መረጃ እጅግ የሚያስገርም ነው፡፡

ከላይ ያየነው ትንታኔና ተመሳሳይ ትንታኔዎች እጅግ በጣም ብዙ ቁጥሮችንና ስታቲስቲካዊ መረጃዎችን ይዘዋል፡፡ ለነገሩ ቁጥሮች እውነታን በአጽንዖት ለማስረዳት በጣም መልካም ናቸው፡፡ ነገር ግን ቁጥሮች ከጀርባ ያለውን የሰውን ልጆች ስቃይና ከፍተኛ መጠን ያለውን ጉዳት አይገልጡም፡፡ ወሲባዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ና እየደረሰባቸው ያሉትን ልጆች ድንጋጤና መከራ ለማወቅ ና ተጨማሪ ምሳሌዎችና ለዚህ ችግር ሰለባ የሆኑትን ልጆች ለመረዳት /ማጣቀሻ 39/ ይመልከቱ፡፡

በዓለማችን ላይ የሚገኙ በርካታ ግብረ ሰዶማውያን ደጋፊ ድርጅቶች ለግብረ ሰዶማዊነት ድርጊት/ልምምድ አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሉ ‹‹የልጆችን ለአካለ መጠን›› የመድረሻ እድሜ ዝቅ እንዲል የሚያስችል መሠረት እየጣሉ ይገኛሉ፡፡ ልጆቻችንን ከወሲብ ጥቃት አፍቃሪዎች የመታደግን አጀንዳ ይዞ የተነሣ አንድም የግብረ ሰዶማዊ ድርጅት (ጌይ ሎቢ) ያለመገኘቱ በጣም የሚያስገርም ነው፡፡ የሆነው ነገር ሁሉ የተገላቢጦሽ ነው፡፡ለነገሩ ግብረ ሰዶማውያን ያልሆኑ (ሄትሮሴክሹዋልሰ) ግን በልጆች ላይ ወሲባዊ ጥቃት የሚያያደርሱ /ፔዳፋይልስ / አሉ፡፡ ነገር ግን በሽተኞች ይመሰሉኛል፡፡ የልጆችን ወሲባዊ ጥቃት ልምምድ በመደገፍ የማስተዋወቅ ስራን እንደሚሰራው የኖርዝ አሜሪካ ማን-ቦይ ላቭ አሶሲየሽ ደፍረው በግልጽ ድርጊቱን ሲያስተዋዉቁ አይታዩም፡፡ ልክ እንደዚሁም በያመቱ የሚከበረውን የግብረ ሰዶማውያንን በዓልን (ጌይ ዴይ) ለማክበር ወደ ታይላንድ እንደሚሄዱት የግብረ ሰዶማውያን ማኅበረሰብ አባላት ግብረ ሰዶማውያኑ ያልሆኑት ማኅበረሰብ የተለየ በዓል የላቸውም፡፡ ታይላንድም በልጆች የሴተኛ አዳሪነት ብዛትና ልማድ ከሌሎቹ ሁሉ አገሮች የተለየች ናት፡፡