ቁጥር 4

ከዶክተር ኒኮሎሲስ ‹‹ ኤ ፓሬንትስ ጋይድ ቱ ፕሪቬንቲንግ ሆሞ ሴክሹዋሊቲ ከተሰኘው

መጽሃፍ የተወሰዱ ጸሁፎች (ማጣቀሻ.4)


‹‹ፖለቲካዊ ትክክለኛነት›› በአዕምሮ ጤና ተቋሞቻችን ሁሉ ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሰ መምጣቱን ቀጥሎአል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1999 በተደረገው የአሜሪካውያን የሳይኪያትሪስቶች አሶሴይሽን ዓመታዊ ጉባኤም ፆታዊ ግንዛቤን በሕክምና ዘዴ መለወጥ ይቻል እንደሆነ ጉዳዩን በአጀንዳው ውስጥ እንዲያካትት ታቅዶ ነበር፡፡ ነገር ግን በስብሰባው ላይ ተጋብዘው የነበሩ ሁለት ተናጋሪዎች ግብረ ሰዶማዊነት ሊለወጥ የሚችል ክስተት ነው የሚለው ጉዳይ ለሳይንሳዊ ጉባኤ የቀረበ ፖለቲካዊ አመለካካት የተጠናወተው ጉዳይ ነው በማለት ስብሰባውን ረግጠው በመውጣታቸው ክርክሩ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ ሳይኪያትሪስት ጀፍሪ ሳቲኖቨርና እኔ በመድረክ ውይይቱ ላይ ተካፋዮች እንድንሆን መጀመሪያውኑ ተጠቁመን ነበር፡፡ ግን ለወንዶች ግብረ ሰዶማውያን ተቆርቋሪ የሆኑ ሳይኪያትሪስቶች እኔም ሆንኩ ሳቲኖቨር በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ከሆንን እንደማይካፈሉ አስታወቁ፡፡

ድኅረ ምረቃ ተቋም ተማሪ ና ግብረ ሰዶማዊነት (ሄትሮሴክሹዋሊቲ) መደበኛ እንደሆነ የምታስብ ሰው ነህን; ያለህን አመለካከትህን ለመግለጥ ፣ መመሪቂያ ጽሑፍን ለማሳተም ፣ ከሥራ-ጓደኞችህ ለመግባባት መልካም እድል ይግጠምህ፡፡ ነገር ግን ይህንን ሐሳብህን ለራስህ ብቻ ብትይዝ ይሻልሃል ያለበለዚያ ግን አንተን ለመቀበሉ ማረጋገጫ እንዲሰጥህ ከምትደክምለት ማህበራዊ ክለብ ውስጥ ተጨፍልቀህ ትወጣለህ፡፡

‹‹ስነልቦና (ሳይኮሎጅ) ከብዙ ነፃ አዕምሮዎች ስብስብ የተሰራ ነው፡፡ ‹‹ሁሉም ለህብር ያለውን ፍቅር እያሰተጋባ፣ሌላው እንደሚያስበው እንድታስብ ተጽዕኖ የሚደረግበት ነው የሚል አባባል አለ፡፡ ለመሆኑ የሙያው ባለቤቶች በዚህ አባባል ምፀት እንዳለ አውቀውት ይሆን; የናሽናል አሶሴይሽን ኦፍ ሪሰርች ኤንድ ቴራፒ /ኤን.ኤ.አር.ቲ.ኤች/ ፕሬዚንት እንደ መሆኔ መጠን፣ የአሜሪካ ሳይኮሎጅካል አሶሴይሽ ፕሬዚዳንት ኖሪን ጆንሰን የምሁራን የአእምሮ ነፃነት በተመለከተ ታዋቂነትን ያገኘ ና ስሜትን የሚነካ የተማጽኖ ጽሁፍ በአንድ ህትመት አምድ ላይ ማቅረቧ ልቤን አደፋፍሮታል፡፡ ክርክሮቹ ሠፊና ብዛት ያላቸው ቢሆኑም በኤ.ፒ.ኤ. ውስጥ የሚደረገውን ገልጽ ክርክር አጥብቄ እደግፋለሁ፡፡ ክርክር፣ጤናማ ነው፡፡ አለመስማማት ጤናማነት ነው፡፡ ውጤታማና ጤናማ ሳይንስ ምንጊዜም ነፃ ምርምር ገና ሐሳብን በነፃነት የመግለጥ መብትን ይጠይቃል፡፡

የጆንሰንን የእንዲህ ዓይነቱ ስሜት-አዘል ንግግር ምክንያት ምድንር ነው; እንዳለ መታደል ሆኖ በፆታዊ ግንዛቤያቸው ለውጥ ስለሚፈልጉ ሰዎች ግድ ብሏት አይደለም፡፡ ዶ/ር ጆንሰን በጣም ግድ ያላት በአሶሲየሽኑ ላይ የተነሳው የሕዝብ ተቃውሞ ነው፡፡ የአሜሪካ ሳይኮሎጅስት አሶሲየሽን /ኤ.ፒ.ኦ/ አንደኛው እትሙ ላይ የወሲባዊ ጥቃት ልማድ ካላቸው ሰዎች ጋር የተደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ጥቃቱ በደረሰበት ልጅ ህሊና ውሰጥ በሚያስገርም ሁኔታ ሁሌም በበጎነቱ የሚታወስ እንደሆነ ጽፏል፡፡ ከሕዝቡ የተነሳውን ነቀፋ ለማርገብ አሶሴይሽኑ በቀረበው ጽሑፍ ላይ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ የዶ/ር ጆንሰንም የሳይንሳዊ ነጻነት ተማጽኖ ጥያቄ በምትኩ በልጆች ላይ የሚደረገውን የወሲብ ጥቃት አመለካካት ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚያደርገውን የደራሲውን መብት ለመደገፍ የተደረገ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ቅራኔዎችን ለመቅረፍ ጆንሰን ባሳየው ፈቃደኛነትና ድፍረት፣ ልክ የግብረ ሰዶም ደጋፊ ድርጅቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ ኤን.ኤ.አር.ቲ.ኤች የኛን ሳይንሳዊ ስብሰባዎች ኤ.ፒ.ኤ. ሕትመቶች ላይ ለማስተዋወቅ በደብዳቤ ጽፎ ፈቃዳችንን ጠይቆን ነበር፡፡ /ኤን.ኤ.አር.ቲ.ኤች የከዚህ ቀደም ጥያቄዎች ተቀባይነት አልነበራቸውም፡፡ በውጤቱም ከኤ.ፒ.ኤ. ፕሬዚዳንት ሳይሆን ከ‹‹ ኦፊስ ኦፍ ጌይሥ፣ሌዝቢያነስ፣ኤንድ ባይሴክሹዋልስ›› ቢሮ ዋና ሃላፊ ከክሊንተን አንደርንስ ምላሽ ተሰጠን፡፡ አንደርሰንም በፖለቲካዊ አቋማቸው የተለዩና ለግብረ-ሰዶማውያን ወንዶች ጥብቅና የቆሙ ቡድኖችን የሚወክል ነው ፡፡ የኤን.ኤ.አር.ቲ.ኤችን በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ያለውን አመለካከት አጥብቆ የሚቃወምና ቅድመ-ግብረ ሰዶማውያን ልጆችን የሕክምና ክብካቤ ሐሳብ ፈጽሞ አጥብቆ ይቃወማል፡፡ የኤን.ኤ.አር.ቲ.ኤችን ደብዳቤ ለአንደርሰን ቢሮ መላክ ማለት በሕግ ማስከበር ስራ ላይ ያለዎትን ቅሬታ ለከተማው ከንቲባ ቢሮ ሲልኩ የከንቲባ ቢሮ ነገሩ መልሶ በፖሊስ እጅ እንዲገባ ለፖሊስ ኮሚሽነር መልሶ እንደሚመራው ይሆናል ማለት ነው፡፡ በእርግጥም እኛም ያቀረብነው ጥያቄም ተሠርዞብናል፡፡

 ኤ.ፒ.ኤ. በእርግጥም ሳይንሳዊ ግልጽነትን የሚፈልግ ቢሆን እንደ ኤን.ኤ.አር.ቲ.ኤች የመሰሉ ድርጅቶችን እንዲካፈሉ መጋበዝ ይገባቸዋል፡፡ ሳይንሳዊ ነፃነትም በሰብዓዊ የፆታ ግንዛቤ ላይ አተረጓጐምና አስፈላጊነት ላይ የተለየ ግንዛቤ ያላቸውን ድርጅቶችን ሁሉ ማካተትን ይጠይቃል፡፡ ሆኖም ለልጆቻቸው ተመሳሰይ-አመለካከት ያለው ሃኪም በማፈላለግ የሚደክሙ ወላጆችም ይህን ጽሁፍ ካገኙ በኋላ ሌሎች አማራጭ አመለካከቶች ተቀብሎ ለማስተናገድ በኤ.ፒ.ኤ. ቢሮ ያሉ በሮች ሁሉ ዝግ መሆናቸውን ማወቅ ይችላሉ፡፡