ቁጥር. 5

በሀመር የምርምር ውጤት ላይ የቀረበ ትችት


ሀመርና ቡድኑ ከአንድ የኤድስ ሕክምና ከሚካሄድበት ፕሮግራም ተረጅ ሰዎች መካከል 76 ግብረ ሰዶማውያን ወንዶችን መልምለው ነበር፡፡ የተመለመሉት ሰዎች ሁላቸውም ቢያንስ አንድ ግብረ ሰዶማዊ ወንድም ያላቸውና በአባታቶቸው ሳይሆን በእናቶቻቸው በኩል ባሉ አጎቶቻቸው ዘንድ ጠንካራ የግብረ ሰዶማዊነት ፆታዊ ግንዛቤ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

የሀመር ቡድንም ይህም ክስተት በኤክስ ክሮሞዞም ( X chromosome) ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ጅን ውስጥ መታዬት ይገባዋል ወደሚል መላምት ላይ ደርሷል፡፡ አንድ ሰው የራሱን የኤክስ ክሮሞሶም( X chromosome) የሚያገኘው ከእናቱ ከሁለት ኤክስ ( X Chromosome ) ክሮሞሶሞች በአንዱ በኩል ሲሆን የዋይ ክሮሞሶም ( Y Chromosome) ደግሞ ከአባቱ ያገኛል፡፡ ምክንያቱም እናቶቻቸው ግብረ ሰዶማውያን ባለ መሆናቸው በእናትየዋ ውስጥ ካሉት ሁለት ዘረ-መሎች (ጅን) አንደኛው በውስጡ የግብረ ሰዶማዊነት ዘረ-መል(ጅን ) /ጌይ ጅን/ ሳይዝ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

ስለሆነም ከጠቅላላው ሕዝብ መካከል ግማሽ የሚሆኑት ወንዶች ልጆች የግብረ ሰዶማዊነት ዘረ-መል (ጅን ተሸካሚ የሆነውን ኤክስ ክሮሞዞም ያላቸው ሲሆን ግማሽ ያህሉ ደግሞ የላቸውም፡፡ ነገር ግን ለናሙናነት ከተመረጡት 40 ጥንድ ግብረ ሰዶማውያን ወንድማማቾች መካከል /ግማሽ የሚያህሉት ማትም 20ዎቹ ብቻ ሳይሆኑ/ በ33ቱ በሙሉ የኪው28 (Q28) ዘረ-መል(ጅን) ላይ ልዩነት የሚታይበት የኤክስ ክሮሞዞም አላቸው፡፡ ይህ ቁጥር /33/ ከተገመተው 50% ማለትም ከ20 በላይ በመሆኑ ብቻ ይህ ልዩ ጅን በውስጡ የግብረ ሰዶማዊነት ፆታዊ ግንዛቤ ይዟል ብለው እንዲገምቱ አድርጓቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በዘረ-መላቸው (ጅን) ውስጥ እንዲህ ዓይነት የይዘት ልዩነት ምልክት የሌለባቸው ቀሪ 7 ጥንድ-ግብረ ሰዶማውያን ወንዶች አሉ፡፡ እነዚህ ግኝቶች እውነተኛ ትክክለኛ ቢሆኑና በቀጣይ ሌሎች ጥናቶች ሊደገሙ /ሊባዙ/ የሚችሉ ቢሆን ኖሮ የተደረሰበት መደምደሚያ ከዚህ ጋር ሊያያዝ ይችል ነበር፡፡ በተለይም ይህ የክሮሞዞም ይዘት ክሮሞዞማል ፓተርን/ አስፈላጊም ግብረ ሰዶማዊነትን ለመፍጠርም እንደ በቂ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡፡ ከ40 ግብረ ሰዶማውያን 7 ጥንዶች እንዲህ ዓይነቱ የክሮሞዞም ይዘት ስላልነበራቸው አላስፈላጊ ነው የሚባለው በዚህ ምክንያት ነበር፡፡

በቂ አይደለምም የሚባለውም በሀመርና ቡድኑ የተመሣሣይ የጀርባ ታሪክ ያላቸውን ግብረ ሰዶማውያን ያልሆኑ ወንድማማቾች ላይ ባደረጉት ቀጣይ ጥናት ከእነዚህ ወንድማማቾች አንዳንዶቹ ተመሣሣይ የጅን መለያዎች በኪው 28 (28 ላይ ታይተውባቸዋል፡፡ እንዲህ መሰሉ የዘረ-መል (ጅን) መለያ ምልክት የግብረ ሰዶማዊነት ዘረ-መል ‹‹የጌይ ጅን›› ትርጉም ነው ብሎ መቀበል አዳጋች ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ምርምር እውነተኛ ቢሆን ኑሮ በዚህ ጅን ውስጥ ከሌሎች ቤተሰባዊ-ባህርያት ጋር ተያያዥነትን የሚፈጥሩና ግለሰቡን ለግብረ-ሰዶማዊነት ዝንባሌ የሚዳርጉ ሌሎች ጥቂት ባህርያት ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ መከራከር ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ የዚህ ዓይነት የጅን መለያ /ጅን ማርኪንግ/ ያለው ግለሰብ ታላቅነት-ፈላጊ ሊያደርገው ለሚችል ጄኒቲካዊ ዝንባሌ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡

ምን ሊሆን እንደሚችል ማን ያውቃል;